በ2023 የትራንስፖርት ዋና እቅድ አማራጮች ላይ የባለድርሻ ምክክር
የአዲስ አበባ ከተማ ስትራቴጂክ ሁለገብ የትራንስፖርት ልማት ዕቅድ ዝግጅት በሂደት ላይ ሲሆን የአማካሪው የባለሙያ ቡድን አራት የትራንስፖርት ዕቅድ አማራጮችን (“ምልከታዎችን”) አዘጋጅቷል፡፡ የአማራጮቹን ግምገማ ተከትሎ ከሕዝብ ምክክር የተሰጡ አስተያየቶችን በማካተት የተሻለውን አማራጭ በማበልጸግ በከተማው ውስጥ የወደፊቱን የትራንስፖርት እቅድ እና ኢንቬስትመንት እንዲመራ ይደረጋል፡፡ አራቱ አማራጮች፦
- የተለመደውን አሰራር የማስቀጠል ምልከታ (Business As Usual (BAU) Scenario): በዚህ የመነሻ አማራጭ ምልከታ ውስጥ የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ሥርዓት እድገት በሂደት ላይ ባሉ ስራዎች ይህም ማለት ከተለመደው የጥገና ሥራ እና ቀድሞውኑ በመገንባት እንዲሁም ጨረታ ላይ ባሉ እና የገንዘብ አቅርቦት የተመቻቸላቸው ወይም በመጨረሻዎቹ የንድፍ ስራ ደረጃዎች ላይ (ጨረታውን በመጠባበቅ ላይ) ባሉ ስራዎች የተገደበ ነው ፡፡ ተግባራዊነታቸውም ሲታይ ከቀረቡት ሌሎቹ አማራጭ ምልከታዎች የጊዜ ሰሌዳ (2023 ዓ.ም) በፊት ሊተገበሩ የሚችሉ ናቸው።
- ተቋማዊ ምልከታ (Institutional Scenario): ይህ ሁለተኛው አማራጭ ምልከታ በአዲስ አበባ የከተማ መዋቅር ዕቅድ እና በሌሎች የፀደቁ ንድፎችና እቅዶች ውስጥ የተካተቱትን ሁሉንም ድርጊቶች እና ማሻሻያዎች ያጠቃልላል፡ ይህም እንደ አዲስ አበባ ሞተር-አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ፡ ያሉትን ያጠቃልላል። እንዲሁም በመጀመሪያው ምልከታ (የተለመደውን አሰራር የማስቀጠል ምልከታ (Business As Usual (BAU) Scenario)) ውስጥ የተካተቱ ከአዲስ አበባ የከተማ መዋቅር ዕቅድ የትግበራ ጊዜ ውስጥ እንደሚገኙ የሚታሰቡ ሁሉም ድርጊቶች እና ማሻሻያዎችን ያጠቃልላል፡፡
- ፖሊሲ ተኮር 1 ምልከታ (PO1): ይህ አማራጭ ምልከታ በትራንስፖርት 2023 ዓ.ም ራዕይ ላይ የተገለጹትን ግቦች ለማሳካት አስፈላጊ ናቸው ተብለው የሚታሰቡትን ሁሉንም ድርጊቶች እና ማሻሻያዎች ያካተተ “ምቹ ምልከታ” ን ለመወከል በ SCTDP ቡድን ተዘጋጅቷል ፡፡ ይህ ምልከታ የመንገድ ደህንነትን ችላ ሳይል የግል ተሽከርካሪ አጠቃቀምን እድገት ደጋፊ የትራፊክ ፍሰት አቅም እና ፍጥነትን ለማቅረብ ከፍተኛ መጠን ያለው የመንገድ ዲዛይን ማሻሻያዎችን ያካትታል፡፡ PO1 የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚደግፍ እና ለሞተር ተሽከርካሪዎች መሰረተ ልማት የበለጠ ትኩረት የሚሰጥና “ባህላዊ የመንቀሳቀስ ዘይቤ” የሚከተል የሙሉ ዕድገት ፖሊሲ ምልከታ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፣ ነገር ግን ለእግረኛ ምቹ አካባቢዎችን፣ ለሞተር አልባ መጓጓዣዎች እና የህዝብ ማመላለሻዎችን ግምት ውስጥ ያስገባ እንዲሁም ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ነጻ እንቅስቃሴ፣ ተደራሽነት እና ደህንነት ዋስትና የሚሰጥ ይሆናል፡፡
- ፖሊሲ ተኮር 2 ምልከታ (PO2): ይህ አማራጭ ምልከታ ከቀዳሚው ጋር ተመሳሳይ ነው፣ ግን እጅግ ያነሰ የመንገድ መሠረተ ልማት ተኮር ነው፡፡ የመንገድ ዲዛይን ማሻሻያዎች መጠን የተጠናከረ ባለመሆኑ ለህዝብ ትራንስፖርት መሠረተ ልማት፣ ለእግረኛ ተስማሚ አካባቢዎች፣ ለሞተር አልባ መጓጓዣዎች መሠረተ ልማት እና ለሞተር-አልባ ተንቀሳቃሽ ቦታ የበለጠ ትኩረት ይሰጣል እንዲሁም ተጋላጭ ለሆኑ የሰዎች ምድቦች ተደራሽነት እና ደህንነት አስፈላጊነት ትኩረት የሰጠ ነው፡፡ ከ PO1 ይልቅ በዚህ ምልከታ ውስጥ የህዝብ ትራንስፖርት ሚና የበለጠ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ እንደ “ዘላቂ እድገት” የፖሊሲ ምልከታ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ይህም “ፈጠራ የታከለበት የእንቅስቃሴ ዘይቤ”ን ይከተላል። ይህ በሁሉም መንገድ “አካታችነት ላይ ያዘነበለ” ምልከታ ነው፣ የትራፊክ ፍጥነቱ እና መጠኑ በተወሰነ መልኩ ለማህበራዊ መደመር እና ለፍትሃዊነት መስዋእት ይሆናል። ከአካባቢያዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መመዘኛዎች አንፃር PO2 የሚመከር አማራጭ መሆኑን በአማካሪዎች የተደረገው ትንታኔ ያሳያል፡፡ ይህ በሚቀጥሉት ዓመታት የአዲስ አበባን ዘላቂ የከተማ ልማት ለመደገፍ የታቀደ ቢሆንም ከፍተኛ ኢንቬስትመንትን የሚጠይቅ ነው፡፡
ቀጣዩ እርምጃ በአራቱ አማራጮች ላይ ከድርጅቶች እና ከህዝብ የተሰጡ አስተያየቶችን መሰብሰብ ነው፡፡ በተለይ PO2ን እንዲመለከቱ እናበረታታዎታለን እናም በሚከተሉት ጉዳዮች እና ተመሳሳይ ይዘት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ግብረመልስ ለመስማት በጣም ፍላጎት አለን፡፡
- ለመንገድ ትራንስፖርት (PO1) ቅድሚያ ከመስጠት ይልቅ እንደ ቀላል ባቡር፣ የአውቶቡስ ፈጣን መጓጓዣ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የብስክሌት ኔትዎርኮች ባሉ ብዙ የህዝብ ማመላለሻ መሠረተ ልማት ውስጥ ባሉ ኢንቨስትመንቶች ምን ይሰማዎታል?
- በ PO2 በተዘረዘሩት የቀላል ባቡር እና የ BRT መንገዶች በቀረቡት ይስማማሉ? ምን መሻሻል አለበት?
- ውስን በሆነ የከተማው ማዕከላዊ ክፍል ውስጥ የመንገድ ኃይል መሙያ ዘዴ ጽንሰ-ሀሳብ ምን ይመስልዎታል? ይህ ወደ ማዕከላዊ አካባቢዎች የሚገቡ የግል ተሽከርካሪዎችን ለመቀነስ የታቀደ ቢሆንም በተጨመሩ የህዝብ ማመላለሻ አማራጮች የሚደገፍ ነው፡፡
- በከተማ ውስጥ የመንገድ ደህንነት ስጋትዎ ምንድነው? የበለጠ የፍጥነት መቆጣጠሪያዎችን እና ደህንነታቸው የተጠበቀ የትምህርት ዞኖችን ይደግፋሉ?
- የጭነት ትራፊክ ትላልቅ የጭነት ተሽከርካሪዎች መሥራት በማይችሉባቸው የተወሰኑ ሰዓታት በመሀል ከተማ ውስጥ በተሻለ ቁጥጥር መደረግ እንዳለበት ተስማምተዋል?