በትራንስፖርት ንዑስ ዘርፍ እቅድ እና ትግበራ ዙሪያ የአጋር አካላት ምክረ ሃሳብ

ለአዲስ አበባ ከተማ ስትራቴጂክ ሁለገብ የትራንስፖርት ልማት ዕቅድ (ኤስ.ሲ.ቲ.ዲ.ፒ.) ማበልጸግ ሥራ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የአማራጮቹን ግምገማ ተከትሎ ከሕዝብ ምክክር የተሰጡ አስተያየቶችን በማካተት የአጋር አካላት አውደ ጥናት በተካሄደበት መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም. የተገኘው ግብረ መልስ ተካቶ እንዲሁም የሕዝብ መረጃ አውድ መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም. የተሻለውን አማራጭ በማበልጸግ የመጨረሻ የስትራቴጂክ ትራንስፖርት ማስተር ፕላን ለከተማዋ ዳብሮ ተዘጋጅቷል፡፡ አማካሪዎች ለንዑስ ዘርፉ እቅዶች (የመንገድ አውታር፣ ሞተር አልባ የሆኑ የትራንስፖርት አማራጮች አውታር፣ የህዝብ ትራንስፖርት አውታር ወዘተ) ተካቶ እንዲሁም ለኤስ.ሲ.ቲ.ዲ.ፒ. የሁሉም ዘርፎች የትግበራ እቅድ ተዘጋጅቷል፡፡

ሁለቱም የንዑስ ዘርፎች እቅዶች እና የትግበራ እቅድ በአማካሪዎች መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ካፒታል ሆቴል ቀርበዋል፡፡

ስለዚህ ፕረዘንቴሽኑን ከዚህ ገጽ ላይ በማውረድ መመልከት የሚቻል ሲሆን የእርሶን ግብረ መልስ ለመስማት በጣም ከፍተኛ ፍላጎት አለን፡፡