የዕቅድ ዝግጅት ተለዋዋጭነት ያለው ሂደት ነው፡፡ ‹ምርጡን› የዕቅድ መፍትሄን ማሳካት የተለያዩ እና ተጣማሪ ታሳቢዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ያለበት ሲሆን ይህም በፖለቲካ ታሳቢዎች፣ የተለያዩ የባለ ድርሻ አካላት ፍላጎቶች እንዲሁም መጠነ ሰፊ የቦታ እቅድ አላማዎች እና ግቦች መካከል ሚዛናዊነትን መፍጠርን ይጠይቃል፡፡ የእቅድ ዝግጅት በጠቅላላ ማህበረሰቡ ላይ ተጽኖ የሚፈጥር ስለሆነ ባለ ድርሻ አካላትን በንቃት የሚያሳትፍ ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው፡፡
ባለ ድርሻ አካላት የሚባሉት ማንኛውም ሰው በሚዘጋጀው ዕቅድ ተጽዕኖ የሚፈጥርበት ሲሆን እና ደግሞ ትራንስፖርት የአዲስ አበባ ከተማ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አኗኗር የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ መጠን በከተማዋ የሚኖር እና የሚሰራ ሁሉም ሰው ባለ ድርሻ አካል ነው፡፡
ለአዲስ አበባ ከተማ አጠቃላይ ራዕይ እና የንዑስ ዘርፍ እቅዶች የተዘጋጁ እንደመሆኑ የአማካሪው ቡድን ዋና ዋና የባለ ድርሻ አካላት ቡድኖችን ለይቶ በማወቅ ለዕቅዱ ግብዓት እንዲሰጡ ይጠይቃል፡፡ በመደበኛነት እውቅና ያገኙ ቡድኖችን ወይም ተቋማትን ጨምሮ የመንግስት መምሪያዎችን፣ የሲቪል ማህበራት ዝግጅቶችን እና መያዶችን፣ ዩኒቨርሲቲዎችን፣ የንግድ ስራ እና የንግድ ስራ ተወካይ ቡድኖችን ያጠቃልላሉ፡፡ ብዙ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች እና መያዶች የተጋላጭ ቡድኖችን/ሴቶችን – ለምሳሌ የአረጋውያን ነዋሪ ተወካይ ቡድኖች፣ የኢትዮጵያ አካል ጉዳት እና ልማት ማዕከልን (ኢሲዲዲን) እና የአዲስ አበባ ሴቶች ማህበርን እንዲወክሉ እና ጥቅማቸውን እንዲያስከብሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይጋበዛሉ፡፡
በተጨማሪም ሁሉም የማህበረሰብ አባላት በታሰቡት የኤስሲቲዲፒ እቅዶች ላይ ግብረ መልስ እንዲሰጡ ይጋበዛሉ፡፡ ሁለት የህዝብ ምክክር መድረኮች የሚዘጋጁ ሲሆን ግብረ መልሶችዎን እና ሃሳቦችዎን በሁለት መንገድ ማቅረብ ይችላሉ፦
- የህዝብ መረጃ መስጫ ክፍለ ጊዜዎች ላይ መሳተፍ እና ግብረ መልስ ለአማካሪ ቡድን በመስጠት፣
- በዚህ ድህረ ገጽ ላይ የሚቀርቡ መረጃዎችንና ሰነዶችን ተመልክቶ ለአስተያየት መስጫ በተዘጋጀው ቦታ ላይ አስተያየት በመስጠት።
ምክክር የሚካሄድበት ጊዜ እና ለህዝብ መረጃ የሚሰጡበት ቦታ በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በዚህ ድህረ ገጽ ላይ ይገለጻል፡፡
ርእይ 2023 ግቦች ክፍል/ቁጥር 2 ላይ … በተጨማሪም በከተማዋ ለአጭር ርቀት የጭነት ሥርጭት cycle delivery (bike cargo)ን በማሰፋፋት ተደጋጋሚ delivery tripን መቀነስ ****ርእዩ ስለ ጭነት ትራንስፖርት sustainability ወይም improvement የሚያወሳው ነገር የለም። የጭነት ትራንስፖርት በተወሰነ መልኩ ቢካተት….. በመንግሥት ደረጃ የተሰጠው ቦታ አናሳ ስለሆነ እዚህ ላይ ካልተካተተ አትኩሮት በማጣት ወደ ከፋ ደረጃ ሊደርስ ስለሚችል attention እንዲያገኝ ርእይ ላይ ብታስገቡት መልካም ነው። የልማት ግቦች እና እርምጃዎች ክፍል/ቁጥር 5 ላይ … ከመሠረተ ልማት አንጻር ግቦች ቢታዩ የሚኒ ባስ ታክሲዎችን ከከተማዋ ለማስወጣት በከተማ አስተዳደሩ ዕቅድ አለ ከዚያ ጋር ተያይዞ ይህ ኢላማ ቢታይ/ቢታሰብበት መልካም ነው። የdigital market ወደ ሀገራችን እየገባ ስለሆነ በሱ ምክንያት የሚፈጠሩ የቤት… Read more »