የአዲስ አበባ ትራንስፖርት
አዲስ አበባ እጅግ ፈጣን መስፋፋት እና የልማት እድገት እየታየባት የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ ምንም እንን የወቅቱ የከተማዋ የነዋሪዎች ብዛት 4.5 ሚሊዮን የሚሆን መሆኑ የሚገመት ቢሆንም አንዳንድ ትንበያዎች ከተማዋ እ.ኤ.አ በ2040 ዓ.ም የነዋሪዎቿ ብዛት 10 ሚሊየን እንደሚሆኑ ይገምታሉ፡፡ የመኪና ባለቤቶች ብዛት መጨመር የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ ልማት እና ሃብት ማደግ የሚያሳይ ቢሆንም ይህ የትራፊክ እና የህዝብ መጨናነቅ ከመፍጠሩም በተጨማሪም ከጤና ደህንነት እና ምርታማናት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ችግሮችን እየፈጠረ ነው፡፡
የኤስሲቲዲፒ ፕሮጀክት
በአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ተግባራዊ የሚደረገውን የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ልማት እቅድ አላማ የአዲስ የትራንስፖርት ከኢኮኖሚ፣ ገንዘብ፣ ቴክኒክ እና አካባቢ እይታዎች አንጻር አዋጭነት ያላቸው እና ባለስልጣናት እና ነዋሪዎችን የሚያሳትፉ ስትራቴጂዎችን እና ፕሮ ክቶችን አቅዶ በመተግበር በከተማዋ ተለይተው የታወቁ የትራንስፖርት እና እንቅስቃሴ ተግዳሮቶችን መቅረፍ ነው፡፡ የዚህ ተልዕኮ ዋና አማካሪ ራምቦል ሲሆን ፕሮ ክቱን ከሞባይሊቲ ኢን ቼይን እና አይአርዲ ኢንጂነሪንግ ከተባሉ ሁለት የጣሊያን ድርጅቶች እና ኤምጂኤም ኮንሰልት ከተባለ የ ገር ውስጥ ንዑስ ስራ አማካሪ ጋር በጋራ ሆኖ ይተገብራል፡፡