የአዲስ አበባ ትራንስፖርት

አዲስ አበባ እጅግ ፈጣን መስፋፋት እና የልማት እድገት እየታየባት የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ ምንም እንኳን የወቅቱ የከተማዋ የነዋሪዎች ብዛት 4.5 ሚሊዮን ይሆናል ተብሎ የሚገመት ቢሆንም አንዳንድ ትንበያዎች ከተማዋ እ.ኤ.አ በ2040 የነዋሪዎቿ ብዛት 10 ሚሊየን እንደሚሆኑ ይገምታሉ፡፡ የመኪና ባለቤቶች ብዛት መጨመር የከተማዋን ኢኮኖሚያዊ ልማት እና ሃብት ማደግ የሚያሳይ ቢሆንም ይህ የትራፊክ እና የህዝብ መጨናነቅ ከመፍጠሩም በተጨማሪም ከጤና ደህንነት እና ምርታማናት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ችግሮችን እየፈጠረ ነው፡፡

በአዲስ አበባ አጠቃላይ የብዙሀን መጓጓዣ ስርዓቶችን ለመፍጠር ጠንካራ የፖለቲካ ፍላጎት አለ፡፡ ከተማይቱ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ አህጉር ያልተለመደ ቀላል የከተማ ባቡር ትራንስፖርት (ኤልአርቲ) ሲስተም አላት፡፡ ከዚህም በተጨማሪም የአውቶቡስ ፈጣን መጓጓዣ መስመር (ቢአርቲ) በቅርቡ ከጀሞ እስከ ዊንጌት በሜክሲኮ፣ ጎፋ እና ጀርመን አደባባይ ከሚሰሩት ጥቂት የውስጥ የአውቶቡስ ማቆሚያዎች ጋር ይገነባል፡፡ ሆኖም ከዚህ የተሻለ የሕዝብ ትራንስፖርት አቅርቦት በቀጣዮቹ 10 አመታት ውስጥ የህዝቡን የትራንስፖርት ፍላጎት ለማሟላት በተሸለ ሁኔታ መቅረብ አለባቸው፡፡ በዚህ መልኩ ከተማይቱ አሁን ያለባትን የትራፊክ መጨናነቅ እና የአየር ብክለትን መቅረፍ ትችላለች፡፡

Addis Public Realm on Streets

በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የህዝብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች፡፡
ምንጭ: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ | ሞተር ላልሆነ የማጓጓዣ ስልት 2019-2028

በአሁኑ ወቅት አስተማማኝ እና አቅምን ያገናዘበ የቀን ተቀን ትራንስፖርት ማግኘት በተለም በዕግር ለሚንቀሳቀሱ ወይም የተጨናነቁ ሚኒባስ ለሚጠቀሙ ከስራ እና ከት/ት ቤት ወደ ጓደኞቻቸው ወይም ወደ ቤተሰቦቻቸው መጓጓዛ ማግኘት የብዙ ሰዎች ህልም ነው፡፡ አብዛኞቹ እርስ በእርስ የሚገናኙ በቀላል ዋጋ የሚገኙ፣ ምቹ፣ ቀጥሎም ለሴቶች እና ህጻናት ተስማሚ እንዲሁም ሁሉንም የሚያሳትፉ የትራንስፖርት አይነቶች ሁሉም የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የትራንስፖርት እድል እንዲያገኙ ማስቻል እና የተሻለ አኗኗር ለመምራት አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የግድ ተግባራዊ መደረግ አለባቸው፡፡

ጥቂቶቹ የከተማዋ እጅግ መሰረታዊ የትራንስፖርት ተግዳሮቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላል፡-

  1. በከተማዋ ባለው የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እጥረት የተነሳ ወደ ስራ ቦታ፣ ትምህርት ቤት፣ የጤና እና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎች መድረስ አለመቻል፣
  2. ተከታታይ የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያዎች መጨመር በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ነዋሪዎች ላይ፣
  3. የመንገድ አቅም እና የትራፊክ ፍሰት ላይ በቅንጅት አለመስራት እና የመንገዶች በእጅጉ መጨናነቅ፣
  4. በቂ የትራፊክ ምልክቶች፣ የመንገድ ምልክቶች እና የመንገድ ላይ ምልክቶች አለመኖር ካሉት የተበላሹ እና በአግባቡ ከማይሰሩ ገጽታዎች ጋር ተደምሮ፣
  5. ተለይትው የተዘጋጁ የአውቶቡስ መንገዶች ወይም የሞተር አልባ መማጓጓዣ መሰረተ ልማቶች እንደ እግረኛ እና የሳይክል መሰረተ ልማት አለመኖር፣
  6. የትራፊክ አደጋዎች ከፍተኛ መጠን፣
  7. አካል ጉዳተኛ ለሆኑ ሰዎች፣ አረጋውያን፣ ሴቶች እና ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ያሉ አማራጮች እጅግ ውስን መሆን፣
  8. ዝቅተኛ የደህንነት እና የጸጥታ ሁኔታ በተለይም በሴቶች ላይ፣
  9. የአየር ብክለት እና የድምጽ ብክለት መጨመር፣
  10. የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት መስጫዎች በበቂ ሁኔታ አለመኖር እና መንገዶች ከመጠን በላይ ለመኪና ማቆሚያ ጥቅም ላይ መዋል፣
  11. አስፈላጊ አገልግሎቶች የተሟሉላቸው የህዝብ እና የጭነት ትራንስፖርት ተርሚናሎች አለመኖር፡፡

በከተማይቱ በፈጣን ሁኔታ እያደገ የሚገኘውን የነዋሪ እና የግል ተሽከርካሪዎች ብዛት ታሳቢ ካደረግን አሁን ለከተማይቱ የበለጠ ዘላቂነት ያለው የትራንስፖርት ስርዓት ለማቀድ እና ቀስ በቀስ ተግባራዊ ለማድረግ ያለው ክፍት መስኮት እድል የተወሰነ ነው፡፡ ይህን እድል በቀጣይ አመታት ካሳለፍነው ከታች ከተመለከቱት ጋር ተያይዘው የከተማዋን የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ዘላቂ ማድረግ በእጅጉ ከባድ እና ከፍተኛ ወጪ የሚያስከትል ነው፡-

  1. የመኪና መጠቀም በከፍተኛ ደረጃ ማደግ፣
  2. መጨናነቅ እና የአየር ብክለት፣
  3. የቦታዎች አለመገናኘት፣
  4. አደገኛ መንገዶች እና የተነጠሉ ዜጎች::