የኤስሲቲዲፒ ፕሮጀክት
በአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ተልዕኮ የተጀመረው የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ልማት እቅድ አላማ የአዲስ አበባን ትራንስፖርት ከኢኮኖሚ፣ ገንዘብ፣ ቴክኒክ እና አካባቢያዊ እይታዎች አንጻር አዋጭነት ያላቸው እና ተሳታፊ በሆኑ ባለስልጣናት እና ነዋሪዎች ተቀባይነት ያላቸው ስትራቴጂዎችን እና ፕሮጀክቶችን አቅዶ በመተግበር በከተማዋ ተለይተው የታወቁ የትራንስፖርት እና እንቅስቃሴ ተግዳሮቶችን መቅረፍ ነው፡፡ የዚህ ተልዕኮ ዋና አማካሪ ራምቦል ሲሆን ፕሮጀክቱን ከሞቢሊቲ ኢን ቼይን እና አይአርዲ ኢንጂነሪንግ ከተባሉ ሁለት የጣሊያን ድርጅቶች እና ኤምጂኤም ኮንሰልት ከተባለ የሀገር ውስጥ ንዑስ ስራ አማካሪ ጋር በጋራ ሆኖ ይተገብራል፡፡
የአዲስ አበባ መጓጓዣ ልማት እቅድ ትግበራ ባለቤትነቱ የአዲስ አበባ ከተማ መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ (አ.አ.ከ.መ.ት.ቢ) ሰፊ የመንገድ መረብ (TRANSIP) ፕሮግራም በአለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የሚተገበር ነው፡፡ ከ2011 የትራንስፖርት ፖሊሲ ልማት በኋላ ትራንስፖርት ቢሮው አቅሙን በማጠናከር ላይ ይገኛል፡፡ አምስት አዳዲስ ተቋማት የተመሰረቱ ሲሆን የነባሩ በአዲስ አበባ ከተማ መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ የነበረው አደረጃጀት ሪፎርም ተደርጓል፡፡ የትራንስፖርት ቢሮው በእቅድ የቀረበውን እና በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገነባውን የአውቶቡስ ፈጣን የትራንዚት ሲስተም እቅድ ማሳደግ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን በተጨማሪም በመንገድ ድር፣ የሕዝብ ትራንስፖርት መሰረተ ልማት እና የጭነት ማጓጓዝ ተግባራትን የመከታተል ኃላፊነት አለበት፡፡
ኤስሲቲዲፒ ፕሮጀክት ከተጀመረበት ከግንቦት 2011 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ አማካሪው የአዲስ አበባን የትራንስፖርት ሁኔታ በጥልቀት ሲተነትን ቆይታል፤ ግኝቶቹንም ለአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ቀጥሎ በቀረቡት የፕሮጀክት ሰነዶች እና አውደ ጥናቶች ላይ ሪፖርት አድርጓል፡፡
- የቅበላ ሪፖርት፤
- በሰኔ 19 እና 20/2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወቅታዊ የአስተዳደር መዋቅሮችን እንዲሁም ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን፣ እድሎች እና ስጋቶችን ጨምሮ ለመረዳት የሚያስቸል የባለ ድርሻ አካላት አውደ ጥናቶች፤ ተገቢ ወቅታዊ እና የታቀደ ህግ፣ ፖሊሲ፣ እቅዶች እና በኤስሲቲዲፒ ከተጠቃለሉ ጉዳዮች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ተዳሰዋል፤
- 4 ጭነት ተኮር የቡድን ውይይት አውደ ጥናቶች፤
- የእቅዶች፣ ደንቦች፣ አስተዳደር እና ተቋማት ክለሳ ሪፖርት፤
- የዳታ አያያዝ፣ ስብሰባ እና ጥቅም ላይ መዋል ሪፖርት።
በሐምሌ ወር 2011 አማካሪው የትራፊክ ዳሰሳ ጥናቶችን እና ቆጠራዎችን በመፈለግ ተጨማሪ አስፈላጊ የትራንስፖርት ውሂቦችን ለመሰብሰብ እና ይህንን መረጃ በመጠቀም በአዲስ አበባ ውስጥ የትራንስፖርት ሁኔታን በጥልቀት ለመገምገም እና የትራንስፖርት ሞዴሉን ለማልማት የመረጃ አሰባሰብ ዕቅድ እና ዘዴን አብራርቷል፡፡ እነዚህ የዳሰሳ ጥናቶች እና ቆጠራዎች ከህዳር አጋማሽ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

ለፓርኪንግ ፍላጎት ጥናት የዳሰሳ ጥናቶች ሥልጠናዎች፡፡
ምንጭ: የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን (ኤኤአርአር)፣ የመኪና ማቆሚያ አስተዳደር እና የትራፊክ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናቶች ለአዲስ አበባ ፣ ሁኔታዊ ትንታኔ ዘገባ ፣ 2019