አዲስ አበባ በዘንድሮው አመት 2011/12 ካላት የ4.6 ሚሊዮን የህዝብ ብዛት በ2022/23 ወደ 7.3 ሚሊዮን እንደሚደርስ የተገመተ በመሆኑ ከተማዋ ዘላቂ የከተማ ትራንስፖርት አውታር ለመዘርጋት የሚያስችላት እቅድ ለማቀድ እና መዋእለ ነዋይ ለማፍሰስ የምትችልበት ደረጃ ላይ ነች፡፡ ሁሉም አካታች ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ያለው ፈጣን፣ ምቹ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያካተተ የትራንስፖርት መሰረተ ልማት እና አገልግሎት ለምጣኔ ሀብታዊ እድገት ወሳኝነት የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም ሆኑ ጎብኚዎች / እንግዶች የትምህርት፣ መዝናኛ እና ጤና ክብካቤ ማዕከላት እንዲሁም ሌሎች የጉዞ ፍላጎቶች ለማሟላት በቀላሉ ተደራሽ ለመሆን አስፈላጊ ነው፡፡

በወቅታዊው የትራንስፖርት ሁኔታ ትንታኔ፣ ተግዳሮት እንዲሁም የወደፊት የህዝብ ቁጥር እድገትና ፍላጎት መሠረት በማድረግ በአለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም በራምቦል ዴንማርክ አማካሪ በመታገዝ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአሁኑ ጊዜ እና በ2022/23 መካከል በአዲስ አበባ የትራንስፖርት የመሰረተ ልማት እና አገልግሎት በምን መልኩ መዘጋጀት አለበት በሚል ርእስ ረቂቅ ጽሁፍ አዘጋጅቷል፡፡ ይህም ቁልፍ የሆኑ ባለድረሻ አካላት ተሳትፎ መሠረት የተዘጋጀ ሲሆን በ6 ቁልፍ ነጥቦች ዙሪያ ልዩ ግብ እና እርምጃዎችን ያካትታል፡፡

  1. ተደራሽ፣ ተመጣጣኝ ዋጋ እና ምቹ የሆነ የህዝብ የመጓጓዣ ስርአት
  2. ፈጣን ምቹ እና ተደራሽ የሚያደርግ የትራንስፖርት ትስስር
  3. ሞተር አልባ ተሽከርካሪዎች እና እግረኞች የሚመራ ምቹ፣ ማራኪ መሰረተ ልማት
  4. በሌላ የትራንስፖርት ስርአት ቅድሚያን የማይወስድ ምቹ እና ውጤታማ የመንገድ ኔትወርክ/መረብ
  5. በከተማይቱ የመንገድ መጨናነቅን እና የደህንነት ችግሮችን የሚቀንስ በተገቢው ሁኔታ ቁጥጥር የሚደረግበት የጭነት መጓጓዣ እና የጭነት መዳረሻ
  6. ተጠያቂነትን እና የረጅም ጊዜ ዘለቄታን ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ የተሻሻለ የትራንስፖርት ዘርፍ መልካም አስተዳደር መኖር ናቸው፡፡

የፕሮጀክቱ ቡድን ሁለት ህዝባዊ የመረጃ ክፍለ ጊዜ በሚኖረው ከረቡዕ 10/3/2012 ጀምሮ በረቂቅ ጽሁፍ ዙሪያ የህዝባዊ ምክክር መድረኩን የሚከፍቱ ይሆናል፡፡ ይህም በሚከተሉት ዝርዝሮች መሰረት በእለተ ረቡዕ 10 እና ሐሙስ 11ኛው ቀን ህዳር ወር 2012 ላይ የሚከናወን ይሆናል፡፡

  • ረቡዕ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም

ሰዓት ከ6፡00 – 11፡00 ሰዓት

ቦታ፡ በኢሊሊ ሆቴል ቢዝነስ ዲስትሪክት ቂርቆስ ክ/ከተማ 17 18 ከጊዮንያ ኮናክሪ ጎዳና አጠገብ ወረዳ 15 አዲስ አበባ (ካርታ ላይ ይመልከቱ)

  • ሐሙስ ህዳር 11 ቀን 2012 ዓ.ም

ሰዓት ከ3፡00-11፡00 ሰዓት

ቦታ፡ በኢሊሊ ሆቴል ቢዝነስ ዲስትሪክት ቂርቆስ ክ/ከተማ 17 18 ከጊዮንያ ኮናክሪ ጎዳና አጠገብ ወረዳ 15 አዲስ አበባ

የማህበረሰቡ አባላት በሙሉ እንዲሁም የህዝባዊ ዘርፍ ድርጅቶች፣ የግል ኩባንያዎች፣ የአካዳሚክ ተቋማት፣ የሲቪል ማህበረሰብ/ሲቪክ ተቋማት፣ ተወካዮች እና ተጠሪዎች እንዲሁም ሌሎች አካላት ከላይ በተጠቀሱት ሰዓታት ውስጥ በህዝባዊ የመረጃ ክፍለ ጊዜ ውስጥ በሚመቻቸው ሰዓት እንዲገኙ ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡

በተመሳሳይ ጊዜ ከህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ የረቂቅ ጽሁፍ (በ https://aatdp.com/consultation/am/)የፕሮጀክቱ ድረገጽ ላይ ማየት የሚቻል ሲሆን ነዋሪዎች፣ የንግድ ማህበረሰብ እንዲሁም ባለድረሻ አካላት በሙሉ በዚሁ የሁለት ሳምንት የምክክር ክፍለ ግዜ ያላቸውን ግብረመልስ እና አስተያየት እንዲሰጡ ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡ ግብረመልስ የመስጠት የጊዜ ገደቡ በእለት ረቡዕ 24/3/2012 ይሆናል፡፡

በሚደርሱት ግብረመልሶች እና አስተያየቶች በሙሉ በትራንስፖርት ልማት እቅድ ቡድን ግምት ውስጥ ገብቶ በታህሳስ 2012 እና ሰኔ 2012 መካከል መዘጋጀት ባለበት የትራንስፖር እቅድ የንኡስ – ዘርፍ ስትራቴጂ ዝርዝር መረጃ ግብአት በማድረግ የሰነቀውን ራእይ በማሻሻል ጥቅም ላይ ያውለዋል፡፡

ተጨማሪ ህዝባዊ ምክክር በ2012 ክረምት ወቅት ሁሉን አካታች ትራንስፖርት እቅድ እና የንኡስ ዘርፍ ስትራቴጂ ለማሟላት የሚረዳ ይሆናል፡፡