የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የዋና ዋና ባለ ድርሻ አካላት ከሰኔ 19 – 20 ያካሄዱት አውደ ጥናቶች

የኤስሲቲዲፒ ቡድን ከአዲስ አበባ ከመንገድ ትራፊክ፣ ከህዝብ ትራንስፖርት እና ከጭነት ትራንስፖርት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወቅታዊ ጠንካራ ጎኖች፣ ደካማ ጎኖች፣ ዕድሎች እና ስጋቶች እንደመገንዘቢያ አንድ ክፍል በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ባለ ድርሻ አካላትን የሚያሳትፉ ሁለት አውደ ጥናቶችን አዘጋጅቷል፡፡ ሁለተኛው አውደ ጥናት በዋነኝት በስርዓተ ጾታ እና የአቃፊነት እሳቤዎች ላይ አተኩሯል፡፡

ወንዶች እና ሴቶች ያላቸው የትራንስፖርት ተሞክሮ በእጅጉ የተለየ በመሆኑ ጠንካራ እቅድ የሴቶችን የምቾት እና የደህንነት ስሜት መፍጠር የሚያስችሉ የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች እና አገልግሎቶች ማምጣት ይኖርበታል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ ለአካለ መጠን የደረሱ ወጣት ወንዶችም በመንገድ ትራፊክ አደጋዎች ተጽእኖ የሚፈጠርባቸው እንደመሆኑ እነዚህን ሂደቶች መገንዘብ የእግረኛ እና የከተማዋን የመንገድ ደህንነትን ለማሻሻል ይረዳል፡፡

ማህበራዊ አቃፊነትም በተጨማሪ የራምቦል መር ቡድን የሚያዘጋጀው የከተማዋ የዘላቂ የትራንስፖርት እቅድ አንዱ ቁልፍ አጀንዳ ነው፡፡ ተጋላጭ እና የተገለሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ለምሳሌ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ ህጻናት ልጆች ያሏቸው ሴቶች እና በከፋ ድህንት ውስጥ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተማ ዋስጥ እንቅስቃሴ ማድረግ ለእነርሱ ከባድ ተግዳሮት በመሆኑ ይህ ትምህረት የመከታተል፣ ስራ የመፈለግ፣ ወይም በከተማዋ አኗኗር ላይ የመሳተፍ እድሎቻቸው እንዲገደቡ ያደርጋል፡፡

አውደ ጥናቶቹ ለቡድኑ ውይይት በሚደረግባቸው የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያሉ ተግዳሮቶች እና መልካም አጋጣሚዎችን ለይቶ ለማወቅ አስችለውታል፡፡ ለምሳሌ፣ ቀልጣፋ የህዝብ ትራንስፖርት ለመፍጠር ጠንካራ የፖለቲካ ፍላጎት አለ እና የቅርብ ጊዜ መሻሻሎቸ እንደ አውቶቡስ ፈጣን ትራንስፖርት (ቢአርቲ) እና የጭነት አሰጣጥ ደንቦች ለቀጣይ ስራዎች ጥሩ መሠረት ይሆናሉ፡፡ ሆኖም ከጥቂት ተግዳሮቶች ውስጥ ቀደም ባሉት ጊዜያት የተሰሩ ስራዎች ምን ያህል ውጠታማ እንደነበሩ የሚያሳይ የመረጃ እጥረት እና ማስረጃ አለመኖር እንዲሁም ትራንስፖርቱ በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የተለያዩ ፍላጎቶች የሚያሟላ ስለመሆኑ የማረጋገጥ አስፈላጊነት፡፡ ቡድኑ በአሁኑ ወቅት በኤስሲቲዲፒ ቡድን በሚሰበሰቡ የትራፊክ እና የእግረኛ ዳሰሳ ጠንካራ የመረጃ መሰረቶች ላይ ተመስርቶ በአሳታፊ፣ ምቹ እና በቀላል ዋጋ የሚቀርቡ የትራንስፖርት አማራጮችን በመጠቀም እነዚህን ተግዳሮቶች የሚቀረፍባቸውን መንገዶች እያጠና ነው፡፡

ተጨማሪ የባለ ድርሻ አካላት ምክክር ዝግጅቶች በተለይም የንዑስ ዘርፉ የትራንስፖርት እቅድ እድገት ደረጃ የተመለከተ መረጃን ለመስጠት በመጪዎቹ ወራቶች ይካሄዳሉ፡፡