የከተማዋን ስትራቴጂካዊ አጠቃላይ የትራንስፖርት ልማት ዕቅድ ለማሳደግ በአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ከተሾመ በኋላ አማካሪው አሁን በአዲስ አበባ መንገድ አውታር ውስጥ በተመረጡ 12 ቦታዎች ላይ የመነሻ-መድረሻ ጥናቶች እያከናወነ ይገኛል፡፡ የመነሻ-መድረሻ ጥናቶች የሚካሄዱት ከአዲስአበባ ትራንስፖርት ቢሮ ፣ ከፖሊስ ኮሚሽን እና ከትራፊክ ቁጥጥር ኤጄንሲ ጋር በመተባበር በሰለጠኑ ተመራቂዎች ነው፡፡

የመነሻ-መድረሻ ዳሰሳ ጥናቶች ከእያንዳንዱ ጉዞ መነሻ እና መድረሻ ጎን ለጎን የተወሰኑ ጉዳዮችን (የጉዞባህሪዎች) ያብራራሉ፡፡ የተሰበሰበው መረጃ የጉዞውን ዓላማ ፣ የተሳፋሪዎችን ብዛት ወይም የጭነትመጠኑን፣ የጉዞውን ጊዜ እና ድግግሞሽ ፣ የጉዞ ጊዜዎችን ፣ ወዘተ የመሳሰሉትን ያጠቃልላል። የመነሻ-መድረሻ ዳሰሳ ጥናት ግኝቶች የከተማውን መልቲ-ሞዳል ትራንስፖርት ሞዴል ለማበልጸግ እንደ ግብዓትያገለግላሉ፡፡ ይህም በትራንስፖርት እቅድ ባለስልጣን በኩል ለሚሰጥ ውሳኔ እንደ መሳሪያነት ያገለግላል፡፡

እስካሁን ድረስ የዳሰሳ ጥናት ቡድን 75% የመረጃ አሰባሰብን አጠናቆ የተቀረው ክፍል ከአንድ እስከ ሁለትሳምንት ጊዜ ውስጥ (በየካቲት 2012 አጋማሽ) ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እባክዎን ማንኛቸውንምየጥናት ባለሙያዎች ካገኙ ለቡድኑ ደጋፊ እና ተባባሪ ይሁኑ፡፡ ከዚህ በፊት በተገነቡት አብዛኛዎቹአካባቢዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሲያሳድር የነበር ሗላ-ቀር የፕላን አሰራር በመተው ለወደፊቱ በአዲስአበባ ውስጥ በተገቢው የተስተካከለ የትራንስፖርት እና የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ አወጣጥ እንዲኖርበማድረግ ለከተማው መልካም ነገር እየሰሩ ናቸው።