በ ‹SCTDP› ፕሮጀክት ላይ የተደረሱ ወሳኝ ምዕራፎች:- የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ራዕይ፣ ግቦች እና የመነሻ ዓመት (Base Year) የትራንስፖርት ሞዴል ፀደቀ።

በትራንስፖርት ማስተር ፕላን ዝግጅት ሂደት ውስጥ 2012/13 ዓ.ም. ሥራ የበዛበት ዓመት ነበር። የ2023/24 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ስትራቴጂክ ሁለገብ ትራንስፖርት ልማት ዕቅድ ፕሮጀክት (SCTDP) ምዕራፍ አንድ የመጨረሻ ውጤት በውጭ አገር አማካሪዎች እና በኢትዮጵያ የትራንስፖርት ባለሙያዎች ቡድን የማዘጋጀቱን ሥራ ቀጥሏል። በ2012 ዓ.ም. በጋ ወራት የትራፊክ እና የቤት ዳሰሳ ጥናቶች ተጠናቀዋል እንዲሁም ለፕሮጀክቱ ሌሎች ጥናቶች፣ ትንተናዎችና ሞዴል ቀረፃዎች ግብአት የሚሆን መረጃ የሚሰጥ የመነሻ ዓመት ባለ ብዙ ሞዳል ትራንስፖርት ሞዴል ተሰርቷል/ተቀርጿል። የነባር የትራንስፖርት ሁኔታዎች እና አፈፃፀም ምዘና እና የ2023/24 ዓ.ም. የትራንስፖርት ራዕይ እና ግቦች አንዱ ቁልፍ አቅርቦት/የመረጃ ግብአት ነው። ይህም ደግሞ ከ2011 ዓ.ም. መጨረሻ ጀምሮ በተከናወኑ የባለድርሻ አካላትና የማህበረሰብ ተወካዮች የምክክር መድረኮች እና ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የቴክኒክ ቡድን በተሰጠ ግብረመልስ እና አስተያየቶች ላይ ተመስርቶ ማስተካከያዎች ተደርጎበታል።

በአሁኑ ጊዜ ለ2023/24 ዓ.ም. ለአዲስ አበባ ከተማ በተዘጋጀ ባለብዙ ሞዳል ትራንስፖርት ትንበያ ሞዴል አማካኝነት እየተፈተሹ ያሉ የተለያዩ የትራንስፖርት ማስተር ፕላን እይታዎች ላይ ከመንግስት እና ከሲቪል ማህበረሰብ ባለድርሻ አካላት ግብረመልስ ለመሰብሰብ በ2013 ዓ.ም. አጋማሽ ጀምሮ የምክክር መድረኮች ታቅደዋል። በመቀጠልም የትራንስፖርት ማስተር ፕላን ረቂቅ ለአስተያየቶች እና ለማሻሻያ ሃሳቦች በፕሮጀክቱ ድህረገፅ አማካኝነት ለህዝብ ግምገማ ተደራሽ ይሆናል። ይህም በፕሮጀክቱ ድህረገፅ እና በማህበራዊ ሚዲያ በኩል ይተዋወቃል።