የዕቅድ ዝግጅት ተለዋዋጭነት ያለው ሂደት ነው፡፡ የመጨረሻውን የዕቅድ ዝግጅት ማሳካት የተለያዩ እና ተጣማሪ ታሳቢዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ያለበት ሲሆን ይህም በፖለቲካ ታሳቢዎች፣ የተለያዩ የባለ ድርሻ አካላት ፍላጎቶች እንዲሁም መጠነ ሰፊ የእቅድ አላማዎች እና ግቦች መካከል ምጣኔ መፍጠርን ይጠይቃል፡፡ የእቅድ ዝግጅት በጠቅላላ ማህበረሰቡ ላይ ተጽኖ የሚፈጥር እንደመሆኑ መጠን ሂደቱ ባለ ድርሻ አካላትን በንቃት የሚያሳትፍ ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው፡፡
ባለ ድርሻ አካላት የሚባሉት ማንኛውም ሰው በሚዘጋጀው ዕቅድ ተጽዕኖ የሚፈጥርበት ሲሆን እና ደግሞ ትራንስፖርት የአዲስ አበባ ከተማ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አኗኗር የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ መጠን በከተማዋ የሚኖር እና የሚሰራ ሁሉም ሰው ባለ ድርሻ አካል ነው፡፡
ለአዲስ አበባ ከተማ አጠቃላይ ራዕይ እና የንዑስ ዘርፍ እቅዶች የተዘጋጁ እንደመሆኑ የአማካሪው ቡድን ዋና ዋና የባለ ድርሻ አካላት ቡድኖችን ለይቶ በማወቅ ለዕቅዱ ግብዓት እንዲሰጡ ይጠይቃል፡፡ እነዚህም የመንግስት መምሪያዎች፣ የሲቪል ማህበራት እና የተራድኦ ድርጅቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የንግድ ስራ እና የንግድ ስራ ተወካይ ቡድኖችን ጨምሮ ቀደም ሲል እውቅና ያገኙ ቡድኖችን ወይም ተቋማትን ያጠቃልላሉ፡፡
በተጨማሪም ሁሉም የማህበረሰብ አባላት በታሰቡት የኤስሲቲዲፒ እቅዶች ላይ ግብረ መልስ እንዲሰጡ ይጋበዛሉ፡፡ ሁለት የህዝብ ምክክር መድረኮች የሚዘጋጁ ሲሆን ግብረ መልሶችዎን እና ሃሳቦችዎን በሁለት መንገድ ማቅረብ ይችላሉ፦
- የህዝብ መረጃ መስጫ ክፍለ ጊዜዎች ላይ መሳተፍ እና ግብረ መልስ ለአማካሪ ቡድን በመስጠት፣
- በዚህ ድህረ ገጽ ላይ የሚቀርቡ መረጃዎችንና ሰነዶችን ተመልክቶ ለአስተያየት መስጫ በተዘጋጀው ቦታ ላይ አስተያየት በመስጠት።
ምክክር የሚካሄድበት ጊዜ እና ለህዝብ መረጃ የሚሰጡበት ቦታ በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ በዚህ ድህረ ገጽ ላይ ይገለጻል፡፡