ፕሮጀክቱ

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን (ኤ.ኤሲአርኤ) በአሁን እና እ.ኤ.አ በ2030 መካከል ያለውን የትራንስፖርት ልማት ለመምራት የአጠቃላይ የትራንስፖርት ልማት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ (ኤስሲቲዲፒ) አዘጋጅቶ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ የትራንስፖርት ዋና እቅዱ በአዲስ አበባ ለሁሉም የትራንስፖርት አይነቶች ለከተማ ትራንስፖርት ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የጉዞ ሞዴል ማልማትን ያጠቃልላል፡፡ እቅዱ በተጨማሪም አዲስ የትራንስፖርት ራዕይ እና በማደግ ላይ ለምትገኘው መዲናቸችን ዘርፈ ተኮር ስትራቴጂዎችን ለይቶ ያስቀምጣል፡፡

የትራንስፖርት እቅዱ የተዘጋጀው ለአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ማስፋፊያ እንደተጨማሪነት ሲሆን የሁሉም የትራንስፖርት አይነት ፕሮጀክቶች ትግበራ እንዲካሄድ ያደርጋል፡፡ ዕቅዱ ከዋና ዋና የሀገር ውስጥ የትራንስፖርት ባለድርሻ አካላት እና ከህዝቡ ጋር በመተባበር እና በመመካከር ይተገብራል፡፡

ፕሮጀክቱ የሚካሄደው በአለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ለሚካሄደው የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ስርዓቶች ማሻሻያ ፕሮጀክት (ቲአርኤኤንኤስአይፒ) ፕሮግራም እንደ አንድ ክፍል ነው፡፡

ተጨማሪ ያንቡ

አማካሪው

ራምቦል ዴንማርክ የፕሮጀክቱ ዋና አማካሪ ሲሆን ስራውን የጀመረው በግንቦት 2011 ዓ.ም ሆኖ እስከ ግንቦት 2013 ዓ.ም ድረስ ስራውን ይቀጥላል፡፡ ራምቦል ፕሮጀክቱን እየተገበረ የሚገኘው ሞባይሊቲ ኢን ቼይን እና አይአርዲ ኢንጂነሪንግ ከተባሉ ሁለት የጣሊያን ድርጅቶች ጋር እና ኤምጂኤም ኮንሰልት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከተባለ የሀገር ውስጥ ምህንድስና ንዑስ አማካሪ ጋር ሆኖ ነው፡፡

የአማካሪው ቡድን ለአዲስ አበባ ከተማ ተመራጭ የሆኑትን የትራንስፖርት እቅድ ስትራቴጂዎችን ለይቶ ለማወቅ እና ለከተማዋ ተስማሚ ሊሆኑ የሚችሉ አማራጮችን ለማቀድ በቪዙም ላይ የተመሰረተ የጉዞ ፍላጎት ሞዴልን በመጠቀም በአዲስ አበባ ከተማ የጉዞ ፍላጎት መዋቅሮች እና የትራንስፖርት ሁኔታዎች ላይ ጥልቅ የዳሰሳ ጥናት ያካሄዳል፡፡ ቪዙም የከተማዋን ፍላጎት የሚያሟላ ትራንስፖርት ለማቀድ ያስችል ዘንድ የከተማይቱን የትራንስፖርት ስርዓት ለመወከል፣ አሁን ያሉትን የትራፊክ ሁኔታዎች በማሳያ ለማቅረብ እንዲሁም የወፊቱን የትራፊክ ፍሰትን ለመተንበይ የሚያገለግል የሶፍትዌር ፓኬጅ ነው፡፡

እንደ ኤስ.ሲ.ቲ.ዲ.ፒ አንድ ክፍል አማካሪው በተጨማሪም ስርዓተ ፆታን እና ሌሎች ተጋላጭ ቡድኖች ይዘቶችን በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የቴክኒክ ክፍሎች ይዘት፣ ትንተና እና ለስርዓተ ፆታ እና ተጋላጭ ቡድኖች ምላሽ ሰጪ/አሳታፊ የትራንስፖርት ሞዴሎች እና መሪ እቅድን ለማሳካት በሚሰጡ የውሳኔ ሀሳቦች ውስጥ ያካትታሉ፡፡ በተቻለ መጠን የስርዓተ ፆታ እና ተጋላጭ ቡድኖች ታሳቢዎች የሚካሄዱት የዳሰሳ ጥናቶች እና ቆጠራዎች ለቪዙም የትራንስፖርት ሞዴል ከስርዓተ ፆታ እና ተጋላጭ ቡድኖች ባህርያት ጋር ተያያዥነት ያላቸው አስፈላጊ መጠነ ዙሪያዎችን መያዝ እንዲችል በአማካሪው የዳታ ስብሰባ እቅድ ስር ይካተታሉ፡፡

ባለ ድርሻ አካላት እና ዜጎች በአጠቃላይ የዕቅድ ዝግጅት ሂደት ወቅት በተለያዩ ባለድርሻ አካላት አውደ ጥናቶች፣ የሕዝብ መረጃ መስጫ ክፍለ ጊዜዎች እና በዚህ ፕሮጀክት ድረ ገጽ አማካኝነት ስለ ፕሮጀክቱ አካሄድ እና ስለ የዕቅዱ ሁኔታ መረጃ ይሰጣቸዋል፡፡

አንዴ እ.ኤ.አ. የ2030 አጠቃላይ የትራንስፖርት መሪ ፕላን ላይ ስምምነት ከተደረሰ በኋላ የትራንስፖርት ንዑስ ዘርፎች ዕቅዶች እና ፕሮጀክቶች በሚኖራቸው የገንዘብ እና ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት ላይ ተመስርቶ ቅደም ተከተል ይዘጋጅላቸዋል፡፡ በሁለተኛው የፕሮጀክት አመት ጥምረቱ ለፕሮጀክቱ ባለ ድርሻ አካላት የራሳቸውን የትራንስፖርት ዕቅድን በማዘጋጀት እና እቅዱን በጊዜ ሂደት ስኬታማ በሆነ መልኩ ለመተግበር የችሎታዎች ሞዴል በማዘጋጀት ረገድ ድጋፍ ያደርግላቸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንቡ

አዳዲስ ዜናዎች

  • Pillars SCTDP
  • Pillars in Amharic

የተደረሱ ወሳኝ ምዕራፎች

January 23rd, 2021|0 Comments

የ2023/24 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ስትራቴጂክ ሁለገብ ትራንስፖርት ልማት ዕቅድ ፕሮጀክት (SCTDP) ምዕራፍ አንድ የመጨረሻ ውጤት በውጭ አገር አማካሪዎች እና በኢትዮጵያ የትራንስፖርት ባለሙያዎች ቡድን . . .

ተጨማሪ ዜናዎች

የፕሮጀክቱ ቡድን

ራምቦል እ.ኤ.አ በ1945 የተመሰረተ ዘርፈ ብዙ ሙያ ባለቤት የሆነ መሪ የምህንድስና፣ የንድፍ እና የማማከር ድርጅት ነው፡፡ ኩባንያው በመላው አለም ከ15,500 በላይ ሙያተኞችን ቀጥሮ ያሰራል፡፡ በ35 ሀገራት ውስጥ በሚገኙ 300 ቢሮዎቹ ራምቦል የሀገር ውስጥ ተሞክሮውን ከአለም አቀፍ መነሻ እውቀት ጋር በማጣመር በደንበኞቻችን፣ የመጨረሻ ተጠቃሚዎች እና በአጠቃላይ ማህበረሰብ ላይ እውነተኛ ልዩነት የሚፈጥሩ መፍትሄዎችን ለማግኘት በትጋት ይጥራል፡፡

ለጥያቄዎ በ48 ሰዓት ውስጥ መልስ እንሰጣለን

ሁልጊዜም ግብረ መልስ እና ጥቆማ ለመስጠት ወይም ጥያቄዎች ለመጠየቅ ቡድኑን ማግኘት ይችላሉ፡፡